80s toys - Atari. I still have
free book gift

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።


Iqra

=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=

ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ


1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።

2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።

3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።

4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
Iqra
Iqra

Homeየወጣቱ ተልዕኮ ምንነትየአቂዳ ትምህርቶችየሶላት መመሪያረመዷንሙስሊም ሴቶችኢስላማዊ ቤተሰብከታሪክ ማህደርሐዲስለወጣቶችትምህርትና መሰረታዊ ክህሎታችጤናችንግጥምጥያቄና መልስኢስላማዊ መዝገበ ቃላት
free book gift

=<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=

ያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም አንብብ!

free book gift

በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው።

free book gift

ለምን ይሆን ሶላት የማንሰግደው


✍ በወጣቱ ተልዕኮ(አህመድ የሱፍ)
Iqra በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

ሶላት ብዙ ጠቀሜታዎች ያሉት ሲሆን ከአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ጋር ያለንን ትስስር ወይም ግንኙንነት የምናጠነክርበት ፣ ለኒዕማዎቹ ሁሉ የምናመሰግንበትና ልቅናውን የምናወሳበት ቢሆንም ብዙ ብዙዎቻችን ወጣቶች ግን አንሰግድም። ልክ አካላችን ምግብና ውሃ እንደሚያስፈልገው ሁሉ ነፍሳችነም መንፈሳዊ የሆኑ ነገሮች ያስፈልጓታልና ራሳችነን በአምልኮት ተግባራት ልናንፅ ይገባል። ከነዚህ የአምልኮት ተግባራት መካከል አንደኛውና ወሳኙ የሆነው ደግሞ ሶላት ነው።

ረሱል(ሰ.ዐ.ወ): አሏህን የሚያወሳና የሚያወሳ ሰው ንፅፅሩ ልክ ህያው እንደሆነ(በህይወት እንዳለ ሰው)ና በሙት ይመሰላል(ልክ እንደሞተ ሰው ነው) ብለዋል።

{ቡኻሪና ሙስሊም}

=<({አል-ቁርአን 8:24})>=


{24} እናንተ ያመናችሁ ሆይ! መልዕክተኛው ህያው ወደሚያደርጋችሁ እምነት በጠራችሁ ጊዜ ለአሏህና ለመልዕክተኛው ታዘዙ። አሏህም በሰውየውና በልቡ መካከል የሚጋርድ መሆኑን ወደ እርሱም የምትሰበሰቡ መሆናችሁን እወቁ።

አንድ ሰው ወደ ጌታው በጣም የበለጠ የሚቀርበው ሱጁድ ላይ በሆነ ጊዜ ነው።

የአሏህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ): ከናንተ መካከከል አንዳችሁ ለሶላት በቆመ ጊዜ ከአሏህ ጋር እየተነጋገረ ነው ብለዋል።

ሶላት በሙስሊሞች ህይወት ውስጥ ግዴታ የሆነ የዘወትር ተግባር ሲሆን ከ5ቱ የእስልምና ምሶሶዎች ውስጥ ሁለተኛውና ወሳኙ የአምልኮት ተግባር ነው። በማንኛውም ሁኔታ ላይ ሁነን ቢሆን እንኴ ቢያንስ በቀን አምስት ጊዜ ልንሰግድ ይገባል። እነዚያ ብርቅየ ሶሃቦች ጦርነት ላይ ሁነው በነበረ ጊዜ እንኴ አሏህ ከሶላት ነፃናችሁ አልነበረም ያላቸው። ይልቁንም እንዲህ ሲል ነበር ያዘዛቸው፦

=<({አል-ቁርአን 2:238-239})>=


{238} ሶላቶቻችሁን ተጠባበቁ በተለይ የመካከለኛይቱ ሶላት(አስር ሶላትን)። ታዛዦች ሁናችሁም ለአሏህ ቁሙ።
{239} ብትፈሩም እግረኞች ወይም ጋላቢዎች ሆናችሁ ስገዱ።

ታዲያ እነዚያ ብርቅየ ሶሃቦች የጦርሜዳ ላይ ሁነው ስገዱ ከተባሉ እኛስ በሰላም ጊዜ እንዴት ብላችሁ ስገዱነው የምንባለው?

መካከል

ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ): የሰው ልጅ በዕለተ ትንሳኤ ከስራዎቹ በመጀመሪያ የሚጠየቀው ስለ ሶላት ነው። ሶላቱ ከተስተካከለ ይሳካለታል። ሶላቱ ያልተሟላ ከሆነ በዕጦት ይሰቃያል(ከከሳሪዎች ይሆናል)፤ ይዋረዳልም ብለዋል።

የአሏህን እርዳታ ሳንሻ ከወንጀል ተግባራትቶች ልንርቅ አንችልም። እንዲሁም ለአሏህ ካለን ፋራቻ ፣ ውዴታና ታዛዥነት የተነሳ ሶላቶቻችነን በወቅቱና በሁሹእ የምንሰግድ ከሆነ ሃራም ነገሮችን አንፈፅምም።

=<({አል-ቁርአን 29:45})>=
{45} ከመፅሐፉ ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ፤ ሶላትንም ደንቡን ጠብቀህ ስገድ። ሶላት ከመጥፎና ከተጠላ ነገር ሁሉ ትከለቀክላለችና።

ሶላት መንፈሳዊ ፍላጎቶቻችነን በማርካት ሰላምና ደስታ እንዲሁም መረጋጋትን ያስገኛል። አሏህ በቁርአኑ በሱረቱል አልረዕድ አንቀፅ 28 ላይ እንዲህ ይላል፦

=<({አል-ቁርአን 13:28})>=


{28} እነዚያ ያመኑ ልቦቻቸው አሏህን በማውሳት የሚረኩ(የሚረጋጉ) ናቸው። ንቁ! አሏህን በማውሳት ልቦች ይረጋጋሉና።

እንደሚታወቀው በዚህ ውስብስብ አለም ውስጥ ወንጀል ከመፈፀም የታቀበ ንፁህ የሆነ ሰው የለም። ደረጃው ይለያያል እንጅ ሁሉም የአደም ልጅ ወንጀል ይሰራል። ከሰው ልጅ ስህተት ከብረት ዝገት አይጠፋም አይደል የሚባለው። ሆኖም አሏህ(ሱ.ወ.ተ) በሶላት ጎዳና ወንጀላችነን የምናሳብስበትን መንገድ አስገኘን። አሏህ በቁርአኑ በሱረቱ ሁድ አንቀፅ 114 ላይ እንዲህ ይላል፦

=<({አል-ቁርአን 11:114})>=


{114} ሶላትንም በቀን በሁለቱ ጫፎች ፣ ከሌሊትም ክፍሎች ፈፅም በእርግጥ መልካም ስራዎች ሃጢያቶችን ያስወግዳልና። ይህ ለተገሳጮች ግሳፄ ነው።

የአሏህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ): ለሶሃቦቻቸው እንዲህ ባሉ ጊዜ ምርጥ ምሳሌ ሰተው ነበር። ከእናንተ መካከል አንዳችሁ በቀን አምስት ጊዜ የሚታጠብበት የሆነ በበራፉ በኩል የሚያልፍ ወንዝ ቢኖረው በሱ ላይ ቆሻሻ ይቀራልን? አሉ። እነርሱም አይቀርም አሉ። የአሏህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ): ልክ እንደዚሁ አሏህ በአምስት አውቃ ሶላቶች ሃጢያትን ያብሳል ሲሉ መለሱ።

ከአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ጋር ያለንን ግኑኝነት ባጠነከርን ቁጥር አሏህ በማንኛውም ነገር ያግዘናል፤ የበለጠም ወደ እሱ ያቀርበናል፤ ችግሮቻችነንም ይፈታልናል። አሏሁ አዘወጀል በቅዱስ ቃሉ በሱረቱል በቀራ አንቀፅ 153 ላይ እንዲህ ይላል፦

=<({አል-ቁርአን 2:153})>=


{153} እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በትዕግስትና በሶላት እርዳታን ሻቱ በእርግጥ አሏህ ከታጋሾች ጋር ነው።

የጀመአ ሶላት ለብቻችን ከምንሰግደው በ25 እጥፍ የሚበልጥ ሲሆን በመካከላችን ወንድማማችነት ፣ እኩልነት እና መተናነስ እንዲያብብ ያደርጋል። ለሶላት በቆምን ጊዜ ዘር ፣ ብሔር ፣ ቀለም ፣ ጎሳ ወ.ዘ.ተ ሳይለያየን አንድ አካል ሁነን ትከሻ ለትከሻ ፣ እግር ለእግር ገጥመን ለአምላካችን አሏህ እናጎበድዳለን።

=<({አል-ቁርአን 82:6})>=


{6} አንተ ሰው ሆይ! በቸሩ ጌታህ ምን አታለለህ?
በመከተል

የመኖራችን ሚስጥር፤ የመፈጠራችን አላማ አሏህን በብቸኝነት መገዛት ሆኖ ያለ እኛ ግን ስሜታችነን አምላካችነን አመፅነው። አሁን መስገድ አለብኝ ከማለት ይልቅ ነገ እሰግዳለሁ ማለትን ስንቅ አድርገን ያዝን። ነገ በህይወት ስለመኖራችን ዋስትናችን ምንድ ነው? ውድ እህት ወንድሞቼ ሆይ! ቆም ብለን እናስብ እባካችሁ! እስኪ በሚከተለው የቁርአን አያ ልብ ብለን እናስተንትን። አሏህ(ሱ.ወ.ተ) በቁርአኑ በሱረቱል መርየም አንቀፅ 59 ላይ እንዲህ ይላል፦

=<({አል-ቁርአን 19:59})>=


{59} ከእነሱም በኋላ ሶላትን የተው ፍላጎቶቻቸውንም የተከተሉ መጥፎ ምትኮች(ትውልዶች) ተተኩ። በእርግጥ የጀሃነምን ሸለቆ ያገኛሉ።

=<({አል-ቁርአን 74:42-43})>=


{42} በሰቀር ውስጥ(በጀሃነም ውስጥ) እንድትገቡ ያደረጋችሁ ምንድነው? ይባላሉ።
{43} እነሱም ከሰጋጆች አልነበርንም ይላሉ።

አሏሁ አዘወጀል ብዙ ዕልቆቢስ የሆኑ ኒዕማዎችን በዙርያችን ሰጠን፤ አስታውሱኝ አስታውሳችኋለሁና አለን፤ ለኔም አመስግኑ አትክዱኝም ሲለን እኛ ግን ፊታችነን ዘወር አድርገን ሶላትን ተውን፤ የአሏህን በረካዎች በልተን እንዳልበላን ሆን። በእርግጥም ይህን በማድረጋችን ከአሏህ ጋር ያለንን ግኑኝነት አቇረጥን።

ውድ እህት ወንድሞቼ እናስተውል! እኛ ስለሰገድን ስላልሰገድን ፣ ስላመሰገነው ስላላመሰገነው አሏህ የሚጎልበት ነገር የለም። እኛ የምንጎዳ ብንሆን እንጅ።

=<({አል-ቁርአን 67:23})>=


{23} እሱ ያ የፈጠራችሁ ለእናንተም መስሚያና ማያዎችን ልቦችንም ያደረገላችሁ ነው። ጥቂትንም አታመሰግኑም በላቸው።

ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ለረጅም ጊዜ ለሶላት በመቆም እግራቸው ያብጥ ነበር። አንዴ ስለዚህ ነገር ተጠይቀው "ለጌታየ አመስጋኝ ባርያ መሆን የለብኝምን?" ሲሉ መለሱ። እኛ ግን አይደለም ቂያመለይል የግዴታ ሶላቶቻችን እንኴ ከብደውናል። እስኪ በልቦቻችን ውስጥ ያለውን ነገር እንፈትሽ!

የሰማያትና የምድር እንዱሁም የፍርዱ ቀን ባለቤት ለሆነው አምላካችን አሏህ ሶላትን ምን ብለን ተውን ነው የምንለው? አሏህ(ሱ.ወ.ተ) 24 ሰዓቶችን ሰቶን ባረባ ነገር ብዙ ጊዜያችነን እያጠፋን ታዲያ ለሶላት እንዴት 15 ደቂቃ አጣንለት?

የአሏህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ): በትንሳኤ ቀን የአደም ልጅ ስለአምስት ጉዳዮች ሳይጠየቅ እግሮቹን አያንቀሳቅስም። ህይወቱን በምን እንዳሳለፈ ፣ ምን በመስራት ወጣትነቱን እንዳሳለፈ ፣ ሃብት ንብረቱን የት እንዳገኘውና በምንላይ እንዳወጣው እንዲሁም ባወቀው ነገር ላይ ምን እንደሰራ ሳይጠየቅ ብለዋል።

ሌላው ማወቅ ያለብን ነገር ብዙ ኡለማዎች ሶላትን የተወ ሰው ከሐዲ ነው ሲሉ ፈትዋዎችን ሰተዋል። ይህም የሚከተለውን ሐዲስ በመጥቀስ ነው።

ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ): በከሐዲዎችና በእኛ መካከል የሚለየን ሶላት ነው። እሷን ችላ ያለ በእርግጥ ካደ ብለዋል።

ሶላት ለመተዋችን የምናቀርባቸው የተለመዱ ምክኒያቶች

ብዙ የሚያረይረብ ነገሮችን እየሰራን፤ ከአንድ ሰዓት በላይ በወሬ እየጨረስን፤ ከአንድ ሰዓት በላይ ሶሻል ሚድያዎችን እየተጠቀምን እንዲሁም ለአንድ ሰዓት ያህል ቻት እያደረግን ለሶላት ጊዜ አጣን? ከሶላት በላይ ጥናታችነን እና ስራችነን እንዴት እናስቀድማለን?

እህት ወንድሞቼ ከማንኛውም ስራ በላይ ሶላትን ነው ማስቀደም ያለብን። ያኔ ሶላታችን ከማንኛውም ነገር በላይ ባስቀደምን ጊዜ አሏህ ሰዓታችነን ይባርክልናል፤ በጥናታችንም ሆነ በስራችን ብቁና ስኬታማ ያደርገናል።

ኒያችነን በማስተካከል በረሱል(ሰ.ዐ.ወ) መንገድ እንተኛ።

ልባችን የፈለገ ያህል ንፁህ ቢሆንም አሏህ እንድንሰግድ ይፈልጋል። ምክኒያቱም የተፈጠርንበት አላማ ይህነውና። በእርግጥ ተግባራችን ወይም ስራችን በልባችን ውስጥ ላለው ነገር ነፀብራቅ ነው። ይሁን እንጅ ከረሱል(ሰ.ዐ.ወ) በላይ ንፁህ ልብ ያለው ማንም የለም። ተወዳጁ የአሏህ መልዕክተኛ ግን እግራቸው እስኪያብጥና እስኪሰነጣጠቅ ድረስ ይሰግዱ ነበር። እኛስ?

በአሏህ ፈቃድ ሶላታችን ከመጥፎና ከተጠላ ነገር ሁሉ ይከለክለናል። ዋናው ከኛ የሚጠበቀው ከልብ በመነጨና ቅን በሆነ ተውባ ወደ አሏህ መመለስ እንዲሁም ሶላት ከመጥፎ ነገር የሚከለክል መሆኑን ከልባችን ማመንናና ሶላቶቻችንን በወቅቱ ከኹሹእ ጋር መስገድ ነው።

Iqra Iqra Iqra Iqra Iqra Iqra Iqra Iqra
453

የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
free book gift

Download Islamic Books
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ

Important Web Links


free book gift

free book gift

free book gift

ስለወጣቱ ተልዕኮ ምንነት ለማወቅ እዚህ ላይ ክሊክ ያድርጉ

Copyright©Youth-Mission የወጣቱ ተልዕኮ